=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
-<({አል-ቁርአን 16:1})>-
«አሏህ የደነገገው እለት ይመጣል፤ እናም ለማፋጠን(ለማቻኮል) አትሹ።»
ክስተቶችን አትሽቀዳደማቸው ፤ ፅንስን ከቀኑ በፊት ማስወረድ ትፈልጋለህ? ፍራፍሬዎችንም ሳይበስሉ መቅጠፍ ትሻለህ? ነገ እውነታነቱ ያልታወቀ ነው አልኖረም ጣዕምም ሆነ ቀለም የለውም። ታዲያ በውስጡ ማለፋችንን ሳናረጋግጥ ስራችንን በሱ የምንፈታው ለምንድነው? ለችግሮቹ የምንሸማቀቀው ፣ ለክስተቶቹ ትኩረት የምንሰጠው ፣ አደጋዎቹን የምንሰጋቸው ለምን ይሆን? ማን ያውቃል ደስታና ዕረፍት የተሞላበት ሆኖ ልናገኘው እንችል ይሆናል። ዋናው ነገር እሱ ገና ወደ ምድሪቱ ያልደረሰ የሩቅ ምስጢር ነው። አንድን ድልድይ ሳንደርስበት ልንሻገር መሞከር የለብንም። ማን ያውቃል ሳንደርስበት እንቆም ይሆናል ወይም ድልድዩ ሳንደርስበት ይፈርስ ይሆናል ፤ ምናልባት ደርሰንበት በሰላም እንሻገርበትም ይሆናል።
ህሊና ስለነገ እንዲያስብ ሰፊ ቦታን መስጠት እና የሩቁን ሚስጥር መፅሃፍ ከፍቶ በአስጨናቂ ስጋቶቹ መተኮስ በኢስላም የተወገዘ ነው። ምክኒያቱም ገደብ የለሽ የተስፋ መኖርን ያመላክታል ፣ ብዙ የዚህ ዓለም ነዋሪዎች ነገ ረሃብ ፣ እርዛት ፣ በሽታ ፣ ድህነት እና አደጋዎች እንደሚገጥሟቸው ያስባሉ። ይህ ሁሉ ከሰይጣን ትምህርቶች ውስጥ ነው።
-<({አል-ቁርአን 2:268})>-
«ሰይጣን እንዳትለግሱ በድህነት ያስፈራራችኋል ፤ በመጥፎም ያዛችኻል። አሏህም ከርሱ የኾነን ምህረትና ችሮታን ሊለግሳችሁ ቃል ገብቷል።»
ብዙ ሰዎች ነገ ስለሚራቡ ከዓመት በኋላ ስለሚታመሙ እና ዓለም ከ 1000 ዓመት በኋላ ስለሚያበቃ ያለቅሳሉ። እድሜው በሌላ አካል እጅ ውስጥ የሆነች ሰው ከሌሉ ነገሮች ጋር ሙግት ሊገጥም አይገባም። መቼ እንደሚሞትም የማያውቅ ሰው እውነታነቱን ካላረጋገጠ የጠፋ ነገር ጋር ጊዜውን ማቃጠል የለበትም። ነገን እስኪመጣልህ ጠብቀው ፤ ስለ ወሬዎቹ አትጠይቅ ፤ ችግሮቹንም አትጠብቅ ምክኒያቱም በዛሬው ስራ ተጠምደሃልና።
መገረም ካማረህ በነዚህ ሰዎች ተገረም ፤ ጭንቀትን ተበደረው ፀሃይ ላልወጣችለት እና ብርሃንን ላላየ ቀን መክፈል ይሻሉ። ተስፋን ከማርዘምም ተጠንቀቅ።
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|